ወደ ማደርያው ገብቼ
✦
ወደ ማደርያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር
ምሥጋናንም ላናቅርብ ስለ ስሙ ክብር
አዝ
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በቤተ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሣለሁ ፪
አዝ
በመከራየ ቀን ሆኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በልልታ ፪
አዝ
ዓሥር አውታር ባለው በበገና
በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምሥጋና
የአፌንም ነገር ሰምተህኛልና ፪
አዝ
ለስሙ ልምበርከክ ለርሱ እንደ ሚገባ
ስዕለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወደ አደባባዩ በምሥጋና ልግባ ፪
አዝ
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ
እንደ ካህናቱ አጆቼን ዘርግቼ ፪
ምሥጋናንም ላናቅርብ ስለ ስሙ ክብር
አዝ
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በቤተ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሣለሁ ፪
አዝ
በመከራየ ቀን ሆኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በልልታ ፪
አዝ
ዓሥር አውታር ባለው በበገና
በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምሥጋና
የአፌንም ነገር ሰምተህኛልና ፪
አዝ
ለስሙ ልምበርከክ ለርሱ እንደ ሚገባ
ስዕለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወደ አደባባዩ በምሥጋና ልግባ ፪
አዝ
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ
እንደ ካህናቱ አጆቼን ዘርግቼ ፪
✦