ወደአንተ እሰግዳለሁ
✦
ወደአንተ እሰግዳለሁ ሳለሁ በሕይወቴ
ለአንተም እገዛለሁ እስከ እለተ ሞቴ
አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘላለም ቤቴ ፪
የነፍስ የሥጋዬ የሕይወቴ ቤዛ
አትበለኝ ችላ በደሌ ቢበዛ
አንተን አምኜ እኖራለሁ ወዴት እደርሳለሁ
አንተን አምኜ እኖራለሁ በአንተም እመካለሁ
ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት
በጽድቅ ጎዳና ልጓዝ ወደፊት
ምራኝ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት፪
ለአንተም እገዛለሁ እስከ እለተ ሞቴ
አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘላለም ቤቴ ፪
የነፍስ የሥጋዬ የሕይወቴ ቤዛ
አትበለኝ ችላ በደሌ ቢበዛ
አንተን አምኜ እኖራለሁ ወዴት እደርሳለሁ
አንተን አምኜ እኖራለሁ በአንተም እመካለሁ
ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት
በጽድቅ ጎዳና ልጓዝ ወደፊት
ምራኝ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት፪
✦