ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል

ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል
ልዩ ነው ክብርሽ ከፍጥረት መሃል
አዝ...
በቃሏ ለማፀን ሳይፈጥራቸው ገና
ታስበሽ የነበርሽ በእግዚአብሔር ህሊና
በሃና ማህፀን ከኢያቄም አብራክ
እናቱ እንድትሆኝ የመረጠሽ አምላክ
አዝ...
ከመላዕክት በክብር አንቺ ትበልጫለሽ
ከሰዎች ልጆች የለም የሚመስልሽ
በእግዚአብሔር ዘንድ ስምሽ የገነነ
አልተገኘም ድንግል እንዳች የከበረ
አዝ...
ነውር የሌለብሽ ንጽሂት ሙሽራ
የመመኪያችን ዘውድ እርተ ህሊና
እናት እና ድንግል ወላዲተ ቃል
የማትለወጪ የሃይማኖት በትር
አዝ...
ከመላዕክት በክብር አንቺ ትበልጫለሽ
ከሰዎች ልጆች የለም የሚመስልሽ
በእግዚአብሔር ዘንድ ስምሽ የገነነ
አልተገኘም ድንግል እንዳች የከበረ
← መዝሙር