ወላዲተ አምላክ
✦
ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል ፪
ልዩ ነው ክብርሽ ፪ ከፍጥረት መሐል
በቃሉ ዓለማትን ሳይፈጥራቸው ገና
ታስበሽ የነበርሽ በእግዚአብሔር ኅሊና
ከሐና ማኅፀን ከኢያቄም አምላክ
እናቱ እነድትሆኝ የመረጠሽ አምላክ
ከመላእክት በክብር አንቺ ትበልጫለሽ
ከሰዎች ልጆችም የለም የሚመስልሽ
በእግዚአብሔር ዘንድ ስምሽ የገነነ
አልተገኘም ድንግል እንዳቺ የከበረ፤
ነውር የሌለብሽ ንጽሕት ሙሽራ
የመመኪያችን ዘውድ ርኅርኅት ልቦና
እንትና ድንግል ወላዲተቃል
የማትለወጪ የሃይማኖት በትር
ልዩ ነው ክብርሽ ፪ ከፍጥረት መሐል
በቃሉ ዓለማትን ሳይፈጥራቸው ገና
ታስበሽ የነበርሽ በእግዚአብሔር ኅሊና
ከሐና ማኅፀን ከኢያቄም አምላክ
እናቱ እነድትሆኝ የመረጠሽ አምላክ
ከመላእክት በክብር አንቺ ትበልጫለሽ
ከሰዎች ልጆችም የለም የሚመስልሽ
በእግዚአብሔር ዘንድ ስምሽ የገነነ
አልተገኘም ድንግል እንዳቺ የከበረ፤
ነውር የሌለብሽ ንጽሕት ሙሽራ
የመመኪያችን ዘውድ ርኅርኅት ልቦና
እንትና ድንግል ወላዲተቃል
የማትለወጪ የሃይማኖት በትር
✦