ወንበዴ ነበርኩኝ

ወንበዴ ነበርኩኝ ሀገር ያስለቸው
በመስቀል ላይ ሆኖ ታሪኬን ለወጠው
አስበኝ ስላልኩት በኋላ ስትመጣ
ገነትን ለማየት የመጀመሪያው ሰው ሆነኩኝ ባለእጣ
አዳም ሕግ አፍርሶ ባመጣው በሽታ
አቤት ፍቅሩ የእግዚእሔር
ግሩም ፍቅሩ ›› ››
ኃያል ፍቅሩ ›› ››
ግሩም ፍቅሩ ›› ››
አስበኝ ስላልኩት አሰበኝ ጌታዬ
ወንበዴ ነበርኩኝ ስርቆት ነው ሙያዬ
በመስቀል ላይ ሆኖ ሕዝቡን ያስብ ነበር
እኔስ አላየሁም እንዲህ ያለ ፍቅር
አልታይም ብዬ ኃጢአትን ስሠራ
ተመለስ ይለኛል ስሜን እየጠራ
እንዳልሞትበት ነው በኃጢአት ታስሬ
ፍቀሩን አልዘልቀውም እንደዚህ ዘርዝሬ
መከራ ሲከበኝ መጥቶ ያጽናናኛል
በሐዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርም ያዝናል
ዓይኑ ከእኔ አይርቅም ጥበቃው አይጠፋም
ስሙን እጠራለሁ በጌታዬ አላፍርም
← መዝሙር