ውበት ነሽ
✦
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
በሃዘን ጠቋቁራ ተከፍታለች ገፄ
አጎንብሻለሁኝ አፈሬ በለምፄ
ወልቋል ከራሴ ላይ የብርሃን ልብሴ
ሃብቴ አንቺ ብቻ ነሽ ያለሽኝ ሞገሴ
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
በሃዘን ጠቋቁራ ተከፍታለች ገፄ
አጎንብሻለሁኝ አፈሬ በለምፄ
ወልቋል ከራሴ ላይ የብርሃን ልብሴ
ሃብቴ አንቺ ብቻ ነሽ ያለሽኝ ሞገሴ
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
ለአምላኬ የማቀርበው አጣሁ በጎ ስራ
ነፍሴ ተጨነቀች በምግባሬ መርራ
ጥላሸቱ በዝቶ ተዳፍኖኗል ጎጆዬ
ብርሃን የለውም ካልበራ ሻማዬ
ነፍሴ ተጨነቀች በምግባሬ መርራ
ጥላሸቱ በዝቶ ተዳፍኖኗል ጎጆዬ
ብርሃን የለውም ካልበራ ሻማዬ
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
የምታመንበት አንዳች ነገር የለኝ
በነፍስም በስጋ ሁሉ የጎደለኝ
እጠባበቃለሁ የእጅሽን በረከት
እቤቴ ላይ አርቦ እስክባረክበት
በነፍስም በስጋ ሁሉ የጎደለኝ
እጠባበቃለሁ የእጅሽን በረከት
እቤቴ ላይ አርቦ እስክባረክበት
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
የጓዳዬ ክብር የቅጥሬ ድምቀት ነሽ
ዓይኔን የምትሞይው በመቅረዜ በርተሽ
የፅልመት ጭላንጭል ጠፍቷል የለም ዛሬ
የብርሃን እናት ስላለች በበሬ
ዓይኔን የምትሞይው በመቅረዜ በርተሽ
የፅልመት ጭላንጭል ጠፍቷል የለም ዛሬ
የብርሃን እናት ስላለች በበሬ
ውበት ነሽ ለቤቴ ለኑሮዬ ፋና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
ድንግል ሆይ አትለይኝ ብቻዬን ነኝና
✦