ውል ውል አለኝ ደጅሽ

ውል ውል አለኝ ደጅሽ
ያምላክ ፈቃድ ሆኖ እስክሳለምሽ
ውል ውል አለኝ ደጅሽ
.
.
የልቤን ፍላጎት ግሸን ላይ ነግሬ፤
ደስታ ቤቴን ሞላው ተረሳ ችግሬ፤
የግሸኗ እመቤት ልኑር በፍቅርሽ፤
ካመቱ ሳትለዪኝ ልቁም ከደጅሽ፤
ውል ውል አለኝ ደጅሽ፤
.
አዝ
.
ሚካኤል ገብርኤል በቀኝ በግራ፤
አንቺ ከመሀል ነሽ ከፍ ባለ ስፍራ፤
የግሸኗ ንግስት ይነገር ዝናሽ፤
ግማደ መስቀሉን በክብር ያኖርሽ፤
ውል ውል አለኝ ደጅሽ፤
.
አዝ
.
(አዝ)
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ
ለመንግስተ ሰማይ ምሳሌ የሆነዉ
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ
.
.
ጉልበቴ በረታ ዳገት ቁልቁለት፤
በምልጃሽ እንዲያገኝ የሀጢያት ስርየት፤
ይናፍቃል ልቤ ደጅሽ እስኪደርስ፤
ፀበልሽን ልጠጣ በእምነት ልታበስ፤
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ፤
.
አዝ
.
የእግዚአብሄር ሀገሩ ግሸን ደብረ ከርቤ፤
እረካሁ ከጥሜ ጠገብኩኝ ከራቤ፤
ሀምሳለ ገነት ነሽ ኢየሩሳሌም፤
አምላክ አክብሮሻል እስከ ዘለአለም፤
ግሸን ሆይ መግቢያሽ አንድ ነዉ፤
.
አዝ
.
የመስቀል ቅርፅ ነው የተራራው ራስ፤
ሁሉም ይናፍቃል ደጅሽ እስኪደርስ፤
ተገልፆ የ'ታየበት የክርስቶስ ፍቅር፤
የእግዚአብሄር አብ መቅደስ አለ በክብር፤
ውል ውል አለኝ ደጅሽ
← መዝሙር