ያ ደሀ ተጣራ

ያ ደሀ ተጣራ እግዚአብሔርም ሰማው
ደርሶ ስላንኳኳ ከጸባኦት እንባው
አምላክ በቸርነት በምህረት ጎበኘው
ባለቀሰ ጊዜ ግራ የገባው ሰው
አዝ ...
መሻት ብቻ ነው የሚፈለግብህ
እግዚአብሔርን ጥራ እመን ትድናለህ
መሻት ብቻ ነው የሚፈለግብህ
እግዚአብሔርን ጥራ እመን ትድናለህ
አዝ ...
ንገረው ችግርክን የውስጥህን ብሶት
ይሽረዋልና አስፈሪውብ ህይወት
ግራ የተጋባው የተከፋው ገፅህ
ይበራል በጸሎት አምላክህን ጠርተህ
አዝ ...
ለወገን ለዘመድ ያስቸገረው መላ
ሲቀልህ ታየዋለህ ካነባህ በኋላ
ሳቅና ንደትህ ይቀራል ይሻራል
በሱ ፈንታ ሰላም ፍቅር ይከብሃል
አዝ...
በከንቱ መጨነቅ እራስን መጥላቱ
ነውና ያጋንንት መግቢያ ምልክቱ
ሀዘን በህሊና በፈሰሰ ጊዜ ንገረው
ለአምላክሕ የልብህን ትካዜ //
← መዝሙር