ያዳነኝን አውቀዋለሁ

ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው
ጨለማዬን አስወግዶ ያበራልኝን አውቀዋለሁ
ሙሉ ሰው ነኝ ከእንግዲህስ ስከተለው እኖራለሁ
የብርሃኔን ልዩ ውበት ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት
ፍቅሩ ማረኮኝ በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት
ላመስግነው ፍቅሩ የማያልቅ ነው
ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው
አሳደረኝ በእቅፉ መጠውለጌን አለምልሞ
በመስቀል ላይ ተሰቀለ ዳንኩኝ እኔ እርሱ ታሞ
በማይዝለው ክንዶቹ ላይ እኔ በክብር እያኖረ
እንዲመቸኝ ዝቅ ብሎ በበረት ውስጥ እሱ አደረ
ላመስግነው ፍቅሩ የማያልቅ ነው
ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው
ቅኔ ባፈስ ምን ይደንቃል ደሙን በመስቀል አፍስሶ
ስለልጁ መዳን ብሎ ነፍሱን ሳይቀር ለኔ ክሶ
ፍቅር ይዞት ከፀባኦት በትህትና ወቶ ወርዶ
ተቀደስኩኝ በነጩ በግ ቀራንዮ ጌታ ታርዶ
ላመስግነው ፍቅሩ የማያልቅ ነው
ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው
አክሊለ ሾክ አጠለቀ ግርማ ክብሩን ሁሉትቶ
አሻገርኝ ወደ ክብሬ በቅዱስ ደም እኔን ዋጅቶ
አጎንብሶ ቀና አረገኝ ፊቴን በፅድቅ እያበራ
እኖራለሁ ለዘላለም ካከበረኝ ጌታ ጋራ
ላመስግነው ፍቅሩ የማያልቅ ነው
ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው!
← መዝሙር