ያደኩት ቤትህ ነው
✦
ያደኩት ፊትህ ነው በቤተ መቅደስ
የኖርኩት ቤትህ ነው በማደሪያህ
አማኑኤል ይጣፍጣል ቃልህ
ጌታዬ ይፈውሳል ስምህ ምስክር ነኝ ልጅህ
ከመንፈስ አብራክ በጥበብ ወለድከኝ
ዘይት እየቀባህ በጸጋ አሳደከኝ
የልጅነት ስልጣን በጥምቀት ተቀበልኩ
አለሁ እስከ ዛሬ ማዕተሜን እንዳሰርኩ እየዘመርኩ
ያደኩት ቤትህ ነው ...............
ብላቴና ሳለሁ ገና በማለዳ
ቃልህን ፃፍክልኝ በልቤ ሰሌዳ
ያሰማህኝ ዜማ ነፍሴን በረበረ
ልቤ ተማረከ ተሸንፎ ቀረ እየዘመረ
ያደኩት ቤትህ ነው ............
ቃኘሁ ጎበኘኋት ዓለምን አየኋት
ብታብረቀርቅም ውስጧ ግን ባዶ ናት
ከኃጥአን ድንኳን ያንተ ቤት ይሻላል
በምድር አክብሮ በሰማይ ያነግሳል ያሸልማል
ያደኩት ቤትህ ነው..............
ዝናውም ይሻራል ይረግፋል ውበቱ
ከሰማዩ በታች ሁሉ የከንቱ ከንቱ
ያንተ መንግስት ግን እስከዘለዓለም ነው
ካንተጋራ መኖር ለኔስ ምርጫዬ ነው ደስታዬ ነው
ያደኩት ቤትህ ነው..............
የኖርኩት ቤትህ ነው በማደሪያህ
አማኑኤል ይጣፍጣል ቃልህ
ጌታዬ ይፈውሳል ስምህ ምስክር ነኝ ልጅህ
ከመንፈስ አብራክ በጥበብ ወለድከኝ
ዘይት እየቀባህ በጸጋ አሳደከኝ
የልጅነት ስልጣን በጥምቀት ተቀበልኩ
አለሁ እስከ ዛሬ ማዕተሜን እንዳሰርኩ እየዘመርኩ
ያደኩት ቤትህ ነው ...............
ብላቴና ሳለሁ ገና በማለዳ
ቃልህን ፃፍክልኝ በልቤ ሰሌዳ
ያሰማህኝ ዜማ ነፍሴን በረበረ
ልቤ ተማረከ ተሸንፎ ቀረ እየዘመረ
ያደኩት ቤትህ ነው ............
ቃኘሁ ጎበኘኋት ዓለምን አየኋት
ብታብረቀርቅም ውስጧ ግን ባዶ ናት
ከኃጥአን ድንኳን ያንተ ቤት ይሻላል
በምድር አክብሮ በሰማይ ያነግሳል ያሸልማል
ያደኩት ቤትህ ነው..............
ዝናውም ይሻራል ይረግፋል ውበቱ
ከሰማዩ በታች ሁሉ የከንቱ ከንቱ
ያንተ መንግስት ግን እስከዘለዓለም ነው
ካንተጋራ መኖር ለኔስ ምርጫዬ ነው ደስታዬ ነው
ያደኩት ቤትህ ነው..............
ዘማሪ ዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ፣ አቤል መክብብ
✦