ያላንተ ጌታ
✦
ያላንተ ጌታ ደስታ መች አለ
ያላንተ አምላኬ ህይወት መች አለ
ስምህን ጠርቶ የተማጸነ
ከእሳቱም ወጣ ከሞትም ዳነ
--
እጆቼን ይዘህ አንተ አየመራ
ስንቱን አለፍኩት ስንቱን መከራ
ለካስ ሲያልፍ ቀን ሁሉም ይረሳል
ረሀብ ስደቱን ማን ያስታውሳል
--
ፅዋዬን ባርከህ ተትረፈረፈ
የጠላቴም ጦር በላይ አለፈ
በሺ ቃላቶች አፌን ሞልቼ
ልዘምርልህ ጉያህ ገብቼ
--
ገዳዬ ቢሮጥ በቀን በማታ
እያለ አንድዬ እያለ ጌታ
ለሞት አልተኛም ይደነቅ አለም
ተክሎኛል ና ለዘለአለም
--
ምስጋና ሆኖ ምግቤ መጠጤ
ተቀጣጠለ ፍቅርህ በውስጤ
አላቀረቅር አልደፋ አንገቴን
እሞላዋለው በልልታ ቤቴን
ያላንተ አምላኬ ህይወት መች አለ
ስምህን ጠርቶ የተማጸነ
ከእሳቱም ወጣ ከሞትም ዳነ
--
እጆቼን ይዘህ አንተ አየመራ
ስንቱን አለፍኩት ስንቱን መከራ
ለካስ ሲያልፍ ቀን ሁሉም ይረሳል
ረሀብ ስደቱን ማን ያስታውሳል
--
ፅዋዬን ባርከህ ተትረፈረፈ
የጠላቴም ጦር በላይ አለፈ
በሺ ቃላቶች አፌን ሞልቼ
ልዘምርልህ ጉያህ ገብቼ
--
ገዳዬ ቢሮጥ በቀን በማታ
እያለ አንድዬ እያለ ጌታ
ለሞት አልተኛም ይደነቅ አለም
ተክሎኛል ና ለዘለአለም
--
ምስጋና ሆኖ ምግቤ መጠጤ
ተቀጣጠለ ፍቅርህ በውስጤ
አላቀረቅር አልደፋ አንገቴን
እሞላዋለው በልልታ ቤቴን
✦