የአብ ቃል አክብሮሽ

የአብ ቃል አክብሮሽ እናት ያደረገሽ
እግዚአብሔር በቃለ ፍጹም ያከበረሽ
የምንመካብሽ መሰላል አንቺ ነሽ
ቅድስና ላንቺ ጽድቅም ላንቺ ሆኖ
ዓለምን የፈጠረ በአንቺ ተወስኖ
የገነት ፍሬ ነሽ ሕይወትን ያፈራሽ
አንቺን ለመረጠ አንቺን ላነጻሽ
ምስጋና ይድረሰዉ ለቸሩ አምላክሽ
አዳም የኖረብሽ የኤዶም ገነት ነሽ
የኤፌሶን ወንዝ ወርቅ የሚፈልቅብሽ
የግዮን ማዕበል ኢትዮጵያን የከበብሽ
ዮርዳኖስን ሆነሽ አሕዛብን ፈወስሽ
በልጁ ቃልነት አብም አከበረሽ
መዓዛሽን ወዶ ወልድ ዋሕድ ዋጅሽ
አብም በሰማያት በኅሊናዉ ሳፈሽ
መንፈስቅዱስ መጥቶ አንቺን አከበረሽ
እመካብሻለሁ እመቤቴ ስልሽ
ወልድ በመዉደዱ ከአንቺ መወለዱን
ንጹሕ ሆኖ አግኝቶት ቅዱሱ ሥጋሽን
ለቃሉ ማደሪያዉ ጽላትና ታቦት
በብሩህ ደመና ተመስለሽለት
ከሥጋሽ ተከፍሎ ከደምሽ ደም ወስዶ
ከነፍስሽም ነፍስ ፍጹም ተዋሕዶ
← መዝሙር