የአባቶች አለቃ ያዕቆብም አለ
✦
የአባቶች አለቃ ያዕቆብም አለ
ለቅሶውም ታደሠ እንባውም አየለ
ለምን አታለቅስ ድንግል ስለልጇ
ስለአሳደገቺው ታቅፎ በእጇ
የስደት መከራ ስለተቀበለች
ከሐዘንም በላይ ድንግል አልቅሳለች
ከልደት ጀምሮ አንስቶ ስቅለቱንም ሳይቀር
ስቃይን ቀምሳለች በምድር ስትኖር
ለተወዳጅ ልጇ እጅግ ለከበረው
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችው
ወልዳ ላልሳመችው ራሔል ስታለቅስ
የድንግል ሐዘንዋ እንዴት እጅግ እንዴት
ይብስ
ከአገር ወደ አገር የተንከራተተች
ድንግል ስለልጇ እጅግ አልቅሳለች
ልብሱን ሲያራቁቱት በዓይኗ በማየትዋ
በሐዘን ተለውሷል የእመቤቴ አንጀትዋ
በሰላሣ ዲናር ልጇን ሊሸጥባት
ይሁዳን በማየት አግብታለች በእውነት
ጌታዋን ሊገድሉ አይሁድ ሲማከሩ
እንባዋ ወረደ ስለግሩም ፍቅሩ፡፡
✦