የአበውን ርስት

የአበውን ርስት አንሰጥም
የአበውን ርስት አንሰጥም አሳልፈን
እንኖራለን ጸንተን መስቀል ተሸክመን
እንኖራለን በእምነት ተደግፈን
ያ እዝራኤላዊው ናቡቴ በሰማሪያ
የወይኑ ፍሬ ናት የማንነቱ መለያ
አክአብ ድምበርተኛው በወይኗ ጎምጅቶ
ነቃቅሎ ሊጥላት ሊያጠፋት ሽቶ
ያቺን መልካም እርሻ ባድማ ሊያደርጋት
ሊገዛት ወደደ በጥፍ ሊለውጣት
አዝ---
ተኩላው ለምድ ለብሶ ገብቶ ከበረትሽ
አድብቶ ሊሰራ እንዲፈርስ ሥርዓትሽ
ለሃይማኖት ቆመን ድል እንነሳዋለን
በርትዕት ተዋሕዶ የኖሩትን ይዘን
አዝ ---
ጠላት ቢከፋብን ያለበደላችን
በብዙ መከራ ቢከበብ ዙሪያችን
በእመብርሃን ምልጃ ሁሉን እናልፋለን
በእግዚአብሔር ቸርነት በርስት እንኖራለን
አዝ---
ዛሬም በእኛ ዘመን አክአብ ተነስቷል
ርስት ድንበራችንን ቀን በቀን ይገፋል
እኛም ናቡቴ ነን ሰማዕት እንሆናለን
የተዋሕዶን ርስት እናስከብራለን
አዝ---
← መዝሙር