የዓለም መድኃኒት የተወለደብሽ
✦
የዓለም መድኃኒት የተወለደብሽ
አንቺ ቤተልሔም የተቀደስሽ ነሽ
የአማልክት አምላክ ንጉሠ ነገሥት
ኃያላን በሙሉ የሚሰግዱለት
በጨርቅ ተጠቅልሎ ተኛ በበረት
የዓለም መድኃኒት -----------------
አዋቂዎች ሁሉ በቅን አሳባቸው
ወደአንቺ ተጓዙ ኮከብ ሲመራቸው፪
የዓለም መድኃኒት ---------------
ለተከታይ ትውልድ ምሣሌ ለመሆን
ሰግደው ገበሩለት ወርቅ እጣን ከርቤን ፪
የዓለም መድኃኒት ------------------
የሚያድለው ጌታ እውቀት ለሕፃናት
የሚመሰገን ነው በአፈ መላእክት
ከእንስሳት ጋራ አደረ በበረት
የዓለም መድኃኒት ----------------
ሥጋ ለብሶ ቢታይ ረቂቅ መለኮት
በአንድ ላይ ዘመሩ ሰውና መላእክት ፪
የዓለም መድኃኒት------------------
አንቺ ቤተልሔም የተቀደስሽ ነሽ
የአማልክት አምላክ ንጉሠ ነገሥት
ኃያላን በሙሉ የሚሰግዱለት
በጨርቅ ተጠቅልሎ ተኛ በበረት
የዓለም መድኃኒት -----------------
አዋቂዎች ሁሉ በቅን አሳባቸው
ወደአንቺ ተጓዙ ኮከብ ሲመራቸው፪
የዓለም መድኃኒት ---------------
ለተከታይ ትውልድ ምሣሌ ለመሆን
ሰግደው ገበሩለት ወርቅ እጣን ከርቤን ፪
የዓለም መድኃኒት ------------------
የሚያድለው ጌታ እውቀት ለሕፃናት
የሚመሰገን ነው በአፈ መላእክት
ከእንስሳት ጋራ አደረ በበረት
የዓለም መድኃኒት ----------------
ሥጋ ለብሶ ቢታይ ረቂቅ መለኮት
በአንድ ላይ ዘመሩ ሰውና መላእክት ፪
የዓለም መድኃኒት------------------
✦