የዓለም ንግሥት የሆንሳ
✦
የዓለም ንግሥት የሆነሽው ድንግል ማርያም እናቴ
ታመሰግንሽ አንቺን ሁልጊዜ ሕይወቴ
ማርያም ባርኪኝ እመቤቴ እሰግድ ለኪ፡፡
እንዳልንገላታ ጠብቂኝ በኃጢአት ዓለም ጎዳና
ደግሞም እንድመገብ ሰማያዊ መና
ማርያም የአዳም ጤና እሰግድ ለኪ፡፡
ተሸጩ ስኖር ልጅሽ በኃጢአት ከተማ ዓለም
የሚያወጣኝ ጠፍቶ የእናት ልጅ ወንድም
ወጣኹኝ በልጅሽ ደም እሰግድ ለኪ፡፡
ከቅድስት ቦታ ሀገር ከቤተልሔም ተነሥተሸ
ምድረ ግብፅ አውራጃ ፈጥነሽ ስትደርሺ
ማርያም መከራን አየሽ እስግድ ለኪ
ያ ምቀኛ ሰይጣን ንጉሥ ተንኮል የተመላው ልጅሽን ሊገለው ደሙንም ለማፍሰስ
ተሯሯጠ በእግር በፈረስ እስግድ ለኪ፡፡
ያንቺ መንገላታት ሁልጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ
በምድረ ግብፅ ሁሉ ያየሽው መከራ
ማርያም ነፍሴን አደራ እሰግድ ለኪ፡፡ ፪
ታመሰግንሽ አንቺን ሁልጊዜ ሕይወቴ
ማርያም ባርኪኝ እመቤቴ እሰግድ ለኪ፡፡
እንዳልንገላታ ጠብቂኝ በኃጢአት ዓለም ጎዳና
ደግሞም እንድመገብ ሰማያዊ መና
ማርያም የአዳም ጤና እሰግድ ለኪ፡፡
ተሸጩ ስኖር ልጅሽ በኃጢአት ከተማ ዓለም
የሚያወጣኝ ጠፍቶ የእናት ልጅ ወንድም
ወጣኹኝ በልጅሽ ደም እሰግድ ለኪ፡፡
ከቅድስት ቦታ ሀገር ከቤተልሔም ተነሥተሸ
ምድረ ግብፅ አውራጃ ፈጥነሽ ስትደርሺ
ማርያም መከራን አየሽ እስግድ ለኪ
ያ ምቀኛ ሰይጣን ንጉሥ ተንኮል የተመላው ልጅሽን ሊገለው ደሙንም ለማፍሰስ
ተሯሯጠ በእግር በፈረስ እስግድ ለኪ፡፡
ያንቺ መንገላታት ሁልጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ
በምድረ ግብፅ ሁሉ ያየሽው መከራ
ማርያም ነፍሴን አደራ እሰግድ ለኪ፡፡ ፪
✦