የአምላክ እናት
✦
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
ድንግል ላወድስሽ ድምፄን ከፍ አድርጌ
አንቺው ነሽ እመአምላክ አክሊለ ማዕረጌ
ስምሽን ስጠራ ጠላት ገለል ይላል
ጉልበት አለሁ ስምሽ ጨካኙን ያራራል
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
ድንግል ላወድስሽ ድምፄን ከፍ አድርጌ
አንቺው ነሽ እመአምላክ አክሊለ ማዕረጌ
ስምሽን ስጠራ ጠላት ገለል ይላል
ጉልበት አለሁ ስምሽ ጨካኙን ያራራል
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
ዶኪማስም ያውራ ያንቺን ምልጃ ፀሎት
እኔም ላወድስሽ የጌታዬ እናት
ከልጅሽ አስታሪቂኝ በተሰጠሽ ፀጋ
ያላንቺማ ለእኔ ምንም የለኝ ዋጋ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
እኔም ላወድስሽ የጌታዬ እናት
ከልጅሽ አስታሪቂኝ በተሰጠሽ ፀጋ
ያላንቺማ ለእኔ ምንም የለኝ ዋጋ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
እግዚአብሔር መርጦሻል ከፍጥረታት ሁሉ
ልዩ ነሽ እናቴ ቤዛዊተ ኩሉ
ምልጃሽ ካልደገፈኝ ዓለም መራራ ናት
አጣፍጪው ድንግል ሆይ መራራውን ሕይወት
ልዩ ነሽ እናቴ ቤዛዊተ ኩሉ
ምልጃሽ ካልደገፈኝ ዓለም መራራ ናት
አጣፍጪው ድንግል ሆይ መራራውን ሕይወት
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
እጠራሻለሁ ዛሬም
እማፀንሻለሁ ዛሬም
✦