የአንተ ሥራ

የአንተ ሥራ ለዓለም ይወራ
በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት
መጻጉዕ ተብሎ ተኝቶ በአራት
ዘመን ያስቆጠረ ሠላሳ ስምንት
ተነሳ ተባለ አገኘ ምሕረት
አዝ----
ሰውነቱ ደቆ እጅግ የታመመ
በእርሱ ድንቅ ሥራ አልጋ ተሸከመ
አዝ---
ወገን ያልነበረው ወድቆ የተረሳ
ምሕረት አገኘና በድንገት ተነሳ
አዝ---
ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ሲናገር
ያልተፈቀደውን ይኸው ሰንበት ሲሽር
አየነው ሰማነው አያሻም ምስክር
ብለው ተነሱበት በጠማማ ምክር
አዝ
← መዝሙር