የአርያም ንግሥት

የሰማይ የምድር የአርያም ንግሥት
አንቺ ነሽ እመቤት የአምላክ እናት
%ኸ ድንግል አማላጅን %ኸ ቅድስት ተራጂን
ለሔዋን ተስፋዋ ለአዳም ዘር ሕይወት
ለደኅነቱ ምክንያት አንቺ ነሽ በእውነት
የኦሪት መጽናኛ ለሐዲስ ኪዳን በር
የወንጌል መሠረት የአምላክ ማኅደር
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የአብርሃም እርሻ የምሥጢር ዋሻዉ
እናትና ድንግል ሁለቱን ሆንሽዉ
የኤፍሬም ዉዳሴ የያሬድ ዉብ ዜማ
የማትጠልቂ ፀሐይ የሃይማኖት ሻማ
← መዝሙር