የአዋጅ ነጋሪ ቃል

የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሀ አየለ
የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳን
ልባችን ለጌ መልካም መንገድ ይሁን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ዐውደ ዓመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሔርን መንገድ እንጥረግ ሁላችን
ማለፊያ እንዲሆነን ወደ አምላካችን
አዝ . . .
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርራኄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ሕይወት እንዲሆን አምላክ ተማጽነናል
አዝ . . .
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችንም አንጻን አደራህ
በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ
አዝ . . .
← መዝሙር