የቤታችን ራስ
✦
የቤታችን ራስ ልጅሽ ነው
አማላጅነትሽ የሚያድነን ነው/2
እመብርሃን፪ሰላም አንቺ እኮ ነሽ ለቤታችን፪
ምን አለንና እኛ በጓዳችን
የጎደለ ነው ይኸው ማድጋችን
ነይ ከልጅሽ ጋር እንድትሞይልን
ድንግል እመቤታችን፪
ያለን ውኃ ነው ከባዶ ጋን ጋራ
የጓሮውም ወይን ብዙም አላፈራ
የደሃ ጎጆአችን እንዲባረክልን
ድንግል አሳስቢልን፪
በሠራኘታ ምድር ታምራት ያደረገ
በኤልያስ አድሮ ሕዝቡን የባረከ
ዛሬም እርሱ ነው የቤቱ ሰላም
አምላክ መድኃኔዓለም፪
ጭንቀትን አይተሽ የልብን ሐዘን
ታሳስቢያለሽ እንዲጎበኘን
እኛም አንቺን ጠርተን ከእፍረት ድነናል
ድንግል ክብር ይገባሻል፪
አማላጅነትሽ የሚያድነን ነው/2
እመብርሃን፪ሰላም አንቺ እኮ ነሽ ለቤታችን፪
ምን አለንና እኛ በጓዳችን
የጎደለ ነው ይኸው ማድጋችን
ነይ ከልጅሽ ጋር እንድትሞይልን
ድንግል እመቤታችን፪
ያለን ውኃ ነው ከባዶ ጋን ጋራ
የጓሮውም ወይን ብዙም አላፈራ
የደሃ ጎጆአችን እንዲባረክልን
ድንግል አሳስቢልን፪
በሠራኘታ ምድር ታምራት ያደረገ
በኤልያስ አድሮ ሕዝቡን የባረከ
ዛሬም እርሱ ነው የቤቱ ሰላም
አምላክ መድኃኔዓለም፪
ጭንቀትን አይተሽ የልብን ሐዘን
ታሳስቢያለሽ እንዲጎበኘን
እኛም አንቺን ጠርተን ከእፍረት ድነናል
ድንግል ክብር ይገባሻል፪
✦