የብርሃን ጎርፍ ናት

የብርሃን ጎርፍ ናት ድንግል እናታችን
ከሰማይ እያበራች ደስ አለው ልባችን
ፍቅርሽን ሰላምሽን ድህነት ይሁነን
ፍጥረት በሙሉ ፊትሽ ይወድቃሉ
ጸጋሽ ይድረሰን ይስጠን እያሉ
የኔ ልብ ምን ፅድቅ አለው አንቺን ለማስተናገድ
የሃጢያት ጎተራ ነው የተሞላ በስስት
ኧረ እንዴት ድንግል ትኑርበት
አትፀየፍም የኔን ልብ ታሰናዳዋለች
ስለሃጢያቴ የኔ እናት ምልጃ ታቀርባለች
ልባቸውን የዘጉ ድንግልን ለማስገባት
ህሊናቸው ይመለስ እንጸልይ ለዚህ ጥፋት
አምላክን ይዛ ነው የምትመጣው
እርሷን ስንመልስ ጌታን ነው የምናስቀይመው
← መዝሙር