የጫማውን ጠፍር

የጫማውን ጠፍር መፍታት የማልችል ነኝ
ይመጣል ከኋላዬ እኔን የሚበልጠኝ
ይመጣል ጌታዬ እርሱ ነው የላከኝ
ይመጣል ጌታዬ እኔኝ የባረከኝ
ከአብ ጋር የነበር ዓለምን ሲፈጥር
ሁሉ በእርሱ ሆኖአል እኔ ነኝ ምስክር
በ 6 ወር እድሜ እኔ እበልጠዋለሁ
በማህፀን ሳለ ለእርሱ ሰግጃለሁ
በማህጸን ሳለሁ ለእርሱ ሰግጃለሁ
መንገዱን ለመጥረግ እኔ ተልኬአለሁ
እርሱ ሊሄድበት አስተካክላለሁ
ጠማማውም ይቅና ጎባጣውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው
የዋህ በግ ክርስቶስ በፊታችሁ ነው
ወደእርሱ ለማድረስ እሰብካሁ እንጂ
መንሹ በእጁ የሆነው እርሱ ነው ፈራጅ
የአዋ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ
ወልደእጓለመህያው ይመጣል እያለ
መጥቶ ሲያጠምቃችሁ በእሳት በመንፈስ
ከአብ ጋር እኩል ነው ከመንፈስ ቅዱስ
← መዝሙር