የዳዊት ሐዘኑ

የዳዊት ሐዘኑ የጴጥሮስ ንስሓ
እኛን ያነጻናል እንደ ንጹሕ ውኃ
ይቅር ባይ ነህና የሰውን በደል
የእኔን አበሳዬን አሁን ይቅር በል
የዳዊት ሐዘን የጴጥሮስ ለቅሶ
የተቀበለ አምላክ ተበድሎ ክሶ
የዛሬም ይቅር በል የሕዝቡን አበሳ
አንተ የከፈልክልን የእኛ ሁሉ አበሳ
በደለኛው እኔ የአንተን ሕግ ጥሼ
ንጹሀ ስጋዬን በጭቃ ለውሼ /
በንስሓ ውሃ አጥቤና ስድሼ
አሁን ይቅር በለኝ መጣሁ ተመልሼ
← መዝሙር