የደናግል መመኪያ
✦
የደናግል መመኪያ
የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ
የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳን
ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን
የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳን
ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ዓውደ ዓመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም፪
ዓውደ ዓመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም፪
ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሔርን መንገድ እንጥረግ ሁላችን
ማለፊያ እንዲሆነን ወደ አምላካችን
አዝ.......................//
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርኅራኄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ሕይወት እንዲሆነን አንተን ተማፅነናል
አዝ.......................//
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችን አንጻን እባክህ
በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ
አዝ.......................//
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሔርን መንገድ እንጥረግ ሁላችን
ማለፊያ እንዲሆነን ወደ አምላካችን
አዝ.......................//
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርኅራኄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ሕይወት እንዲሆነን አንተን ተማፅነናል
አዝ.......................//
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችን አንጻን እባክህ
በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ
አዝ.......................//
✦