የእለት የዓመት

ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
የሰው ልጆች እድሜ ጥንቱንም ሲጀመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንደአንተ አቆጣጠር
አዝ . . .
ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ደካማ ነውና ሰው እድሜ ከራበው
አዝ . . .
እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማይን በኮከብ
እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ
አዝ . . .
ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላ ዓለምን ብገዛ
አዝ . . .
በከንቱ ጊዜያችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በርትተን ከሠራን ያለአንዳች ነቀፋ
አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ
አዝ . . .
← መዝሙር