የእኛ ጌታ
✦
ይእኛ ጌታ የኛ መድኅን
በቸርነትህ ታደገን እኛ እንደሆን ኃይል የለን ፪
ጠዋት ለምልማ ታማ ጠፋች
የሰዉ ኅሊና እያባባች
ዓለም ምኗ ነዉ የጣፈጠን
እያሳሳቀ የወሰደን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ዛሬ አለሽ ሲሏት ትጠፋለች
ከነተንኮሏ ዓለም ሟች ነች
እሾህ በቅሎባት እሾህ ሆና
በመተላለፍ ሰዉ ሊያልቅ ነዋ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ከእኛ ጋር ያለዉ ኃይል ነዉ
በሥጋዊዉ ዓይን ባናየዉ
የጦሩ ብዛት መቼ ያድናል
የዓለም ጥንስስ ተዋሕዷል
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
እንደሰዉ ጥበብ ጥበበኛ
እንደሰዉ ወደር ወደረኛ
እንደ ዓለም ጉልበት ጉልበተኛ
በአምላክ ፊት ሲታይ ሕመምተኛ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
በቸርነትህ ታደገን እኛ እንደሆን ኃይል የለን ፪
ጠዋት ለምልማ ታማ ጠፋች
የሰዉ ኅሊና እያባባች
ዓለም ምኗ ነዉ የጣፈጠን
እያሳሳቀ የወሰደን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ዛሬ አለሽ ሲሏት ትጠፋለች
ከነተንኮሏ ዓለም ሟች ነች
እሾህ በቅሎባት እሾህ ሆና
በመተላለፍ ሰዉ ሊያልቅ ነዋ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ከእኛ ጋር ያለዉ ኃይል ነዉ
በሥጋዊዉ ዓይን ባናየዉ
የጦሩ ብዛት መቼ ያድናል
የዓለም ጥንስስ ተዋሕዷል
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
እንደሰዉ ጥበብ ጥበበኛ
እንደሰዉ ወደር ወደረኛ
እንደ ዓለም ጉልበት ጉልበተኛ
በአምላክ ፊት ሲታይ ሕመምተኛ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
✦