የፍቅር እናት

የፍቅር እናት የሰላም
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
በሕይወቴ ውስጥ በኑሮዬ
ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ
ተደላደለ ልቤ
አንቺ አለሽና ከአጠገቤ
የፍቅር እናት የሰላም
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
ምኞቴም ይስመር ድብቅ ሕልሜ
ልለፍ ወጀቡን ተቋቁሜ
የጌታዬ እናት ነሽ
ኃይልን ያደርጋል ጸሎትሽ
የፍቅር እናት የሰላም
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
እንዴት እቀራለሁ ከመንገድ
አደራ እናቴ አስቢኝ
ለሚያስጨንቀኝ ጠላት
ለሚያሳድድ አትስጪኝ
የፍቅር እናት የሰላም
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
ትላንትም ዛሬም አመሥጋኝ ነኝ
የለም ለነገ የሚያስፈራኝ
ሜዳ ይሆናል ተራራ
ልጅሽ ስላለ ከእኔ ጋራ
የፍቅር እናት የሰላም
ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም
← መዝሙር