የፍቅርህን ጥግ

የፍቅርህን ጥግ ባልደርስበትም
ተመስገን ማለት አላቋርጥም
አንተን ማምለክ ነው የእኔ ስራዬ
በሰማይ በምድር ላለህ ጌታዬ
በበረት አየንህ ወርደህ ተወልደህ
ዓለሙን ሁሉ እንዲሁ ወደህ
ፍቅርህን ሳስብ እደነቃለሁ
በሞትህ ደግሞ እገረማለሁ
አዝ...........
ለድኅነተ ዓለም ቤዛ ሆነሃል
ለኃጥያት ሥርየት ተሰውተሃል
ማዳንህ ብዙ ፍቅርህ ብዙ ነው
ቃላት አይገልጡት ያንተስ ልዩ ነው
አዝ...........
ዓለምን ቀድመህ ከፈጠርክበት
እጅግ ይረቃል ኃላ ያዳንክበት
የብርሃን አምላክ የሕይወት መገኛ
ሞትን ዘለፍከው ሞተህ ስለኛ
አዝ..........
አየን ዳሰስንህ ቃል ሥጋ ሆነህ
ተገለጥክልን በዝግ ቤት ገብተህ
ለዓለሙ ሁሉ የመሰከርንህ
ፍፁም ሰውና ፍፁም አምላክ ነህ
አዝ..........
‘’ ሲሳይ ወልደአረጋይ
ዘማሪ ሲሳይ ወልደአረጋይ፣ ለምለም ከበደ
← መዝሙር