የሀብከ ዮም

የሀብከ ዮም የሀብከ መድኃኔዓለም
ዕድሜ ማቱሳላ ወአብርሃም
ይስጣችሁ ዛሬ ይስጣችሁ መድኃኔዓለም
ዕድሜ ማቱሳላ የአብርሃም
በቅዱስ ጋብቻ ሙሽሮች የተወሰናችሁ
ክርስቶስ ተገኝአል በመካከላችሁ
የድንጋዮቹን ጋን ወይኑን ወይን ሊሞላበት
ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝአል ከዚህ ቤት
ደስታዉን አይቶ አምላክም ፍጹም ተደስአል
ሊባርካችሁም እጆቹን ዘርግአል
በሕይወታችሁም ፍቅር ፍቅር ቅመም ሆኖ
ትሕትናን ይሰጣችሁ እግዚአብሔር በቶሎ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ሠርጋችሁ እንዲሆን ደስታ ፍቅር የተሞላበት
በሕይወታችሁ ዉስጥ ክርስቶስ ይግባበት
በሕይወታችሁ ዉስጥ አምላክ ይኑርበት
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የበረከት ፍሬ በጸጋዉ እንዲበዛላችሁ
ዛሬ& ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ
እራስን በማገዛት ዕዉቀት ለመላችሁ
ዛሬ ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ
በሥጋ ወደሙ እግዚአብሔር ስለመረጣችሁ
የመንፈስቅዱስም ሕፃናቶች ናችሁ
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
← መዝሙር