የሕይወቴ መታመኛ
✦
የሕይወቴ መታመኛ የነፍሴ ተስፋ ጌታዬ አምላኬ
መድኃኔዓለም ላመስግንህ እጠግባለሁ በውዳሴህ
መድኃኔዓለም ላመስግንህ እጠግባለሁ በውዳሴህ
መላእክት በሰማያት ቅዱስ ፫ አንተ ነህ እያሉ
በክንፋቸው አሸብሽበው
ይጠሩሃል በዝማሬያቸው፪
በክንፋቸው አሸብሽበው
ይጠሩሃል በዝማሬያቸው፪
ቅዱስ ዳዊት በበገና ከእሥራል ሀገር፪
በተመስጦ ወደ አርያም ዘልቆ
ዘመረልህ አንተነትህን አውቆ፪
በተመስጦ ወደ አርያም ዘልቆ
ዘመረልህ አንተነትህን አውቆ፪
ሕፃናትም አንተን አምነው
በአህያ ተቀምጠህ ስትመጣ፪
አፍ አውጥተው አመሰገኑ
ሆሣዕና በአርያም አሉ፪
በአህያ ተቀምጠህ ስትመጣ፪
አፍ አውጥተው አመሰገኑ
ሆሣዕና በአርያም አሉ፪
ሃሌ አለ ቅዱስ ዳዊት
ጸናጽል መቋሚያ አንሥቶ፪
ምስጋናህን በልቡ ሽቶ
በመንፈስህ በአንተ ተመርቶ፪
ጸናጽል መቋሚያ አንሥቶ፪
ምስጋናህን በልቡ ሽቶ
በመንፈስህ በአንተ ተመርቶ፪
ፈለጉንም ተከትለው
ካህናት በሙሉ ቆመው፪
ይቀኛሉ ለቅዱስ ስምህ
በማኅሌት በመመስገኛህ፪
ካህናት በሙሉ ቆመው፪
ይቀኛሉ ለቅዱስ ስምህ
በማኅሌት በመመስገኛህ፪
እስትንፋስም ያለው ሁሉ
ያመስግንህ አንተን በእውነት ፪
ከልብ ሆኖ በንጹሕ እምነት
እንደ ዕዝራ እንደ ዳዊት፪
ያመስግንህ አንተን በእውነት ፪
ከልብ ሆኖ በንጹሕ እምነት
እንደ ዕዝራ እንደ ዳዊት፪
✦