የሉም ሞተዋል ሲሉን ኖረን
✦
የሉም ሞተዋል ሲሉን ኖረን
የሉም ጠፍተዋል ሲሉን በዝተን
አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን
አለን በጌታ ሁሉን አልፈን ፪
የሉም ጠፍተዋል ሲሉን በዝተን
አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን
አለን በጌታ ሁሉን አልፈን ፪
ለካስ ሰው ስለሮጠ አይቀድምም
ጉልበታም ስለታገለ አይጥልም
ጎልያድ ወድቋል በዳዊት ጠጠር
የእኛ አምላክ ስሙ ከፍ ይበል ይክበር
እግዚአብሔር ስሙ ከፍ ይበል ይክበር
ጉልበታም ስለታገለ አይጥልም
ጎልያድ ወድቋል በዳዊት ጠጠር
የእኛ አምላክ ስሙ ከፍ ይበል ይክበር
እግዚአብሔር ስሙ ከፍ ይበል ይክበር
ጨክነን እኛ ሰይፉን ባንመዝዝም
በእጃችን ጦር ጎመድን ባንይዝም
ይዋጋል ዝም አይልም እግዚአብሔር
ልጆቹን ፈጥሮ አይሰጥም ለፍጡር፪
በእጃችን ጦር ጎመድን ባንይዝም
ይዋጋል ዝም አይልም እግዚአብሔር
ልጆቹን ፈጥሮ አይሰጥም ለፍጡር፪
በሚነድ እሳት መሐል ሆነን
አልሞትንም ዛሬም በሕይወት አልን
ያልሰማ ሁሉ ይስማ ይግረመው
ያመለክነው እግዚአብሔር እንዲህ ነው፪
አልሞትንም ዛሬም በሕይወት አልን
ያልሰማ ሁሉ ይስማ ይግረመው
ያመለክነው እግዚአብሔር እንዲህ ነው፪
አሕዛብ ዝክራችንን ሊያጠፉ
ቢደክሙ ብዙ ዘመን ቢለፉ
ከአሸናፊዎች ሁሉ በልጠን
አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን
ቢደክሙ ብዙ ዘመን ቢለፉ
ከአሸናፊዎች ሁሉ በልጠን
አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን
✦