የማላልፈው የለም
✦
የማላልፈው የለም ሁሉን አልፈዋለሁ
የአባቶቼን አምላክ ጌታን ይዤዋለሁ
እግሮቼን ለወጥመድ አይሰጥም ጨካኝ ኖ
የወደቀ የለም በስሙ ተማምኖ
የአባቶቼን አምላክ ጌታን ይዤዋለሁ
እግሮቼን ለወጥመድ አይሰጥም ጨካኝ ኖ
የወደቀ የለም በስሙ ተማምኖ
የትናንቱ ፈታኝ የሕይወት እንቅፋት
ዛሬ ተወግዷል በአምላኬ ቸርነት
የምታመንበት ስምህ ጋሻዬ ነው
እግዚአብሔር አለቴ የፀና ግንብ ነው
ዛሬ ተወግዷል በአምላኬ ቸርነት
የምታመንበት ስምህ ጋሻዬ ነው
እግዚአብሔር አለቴ የፀና ግንብ ነው
ድምፅህን ሰምቼ ግብፅን ጠልቻለሁ
ጉልበቴ በርትቶ ተከትየሃለሁ
ወገኔን ቢከድን የፈረኦን ቀንበር
አሰብከን እግዚአብሔር በመጠጋት ምድር
ጉልበቴ በርትቶ ተከትየሃለሁ
ወገኔን ቢከድን የፈረኦን ቀንበር
አሰብከን እግዚአብሔር በመጠጋት ምድር
ፊትና ኋላየን ቢያጥርብኝ ጠላቴ
ብደክም ብተክዝ ብትዝል ሕይወቴ
ሲደርስ ወደሰማይ ለቅሶና እንባዬ
ሰማሄኝ እግዚአብሔር እሩሩ ጌታዬ
ብደክም ብተክዝ ብትዝል ሕይወቴ
ሲደርስ ወደሰማይ ለቅሶና እንባዬ
ሰማሄኝ እግዚአብሔር እሩሩ ጌታዬ
ቀስቱ አልፎ ወድቋል በሕይወት ቆምያለሁ
የአባቶቼን አምላክ አመሰግነዋለሁ
የሞቴን ደብዳቤ ዛሬ ተለውጧል
ጌታ ቸርነቱን በሕይወቴ ገልጧል
የአባቶቼን አምላክ አመሰግነዋለሁ
የሞቴን ደብዳቤ ዛሬ ተለውጧል
ጌታ ቸርነቱን በሕይወቴ ገልጧል
✦