የማትመረመር
✦
ልዑል ልዑል ዲበ ኪሩቤል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ምድር መረገጫህ ሰማይ ዙፋንህ
ምሉዕ በኩለሄ ወሰን የሌለብህ
አልፋና ኦሜጋ የማትመረመር
የውቅያኖስን ውኃ በእጅህ የምትሰፍር
ረቂቅ ባሕርይ ግሩም እግዚአብሔር
ምሉዕ በኩለሄ ወሰን የሌለብህ
አልፋና ኦሜጋ የማትመረመር
የውቅያኖስን ውኃ በእጅህ የምትሰፍር
ረቂቅ ባሕርይ ግሩም እግዚአብሔር
ልዑል ልዑል ዲበ ኪሩቤል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
የሰው ልጅ ጥበቡ የማይደርስበት
የማይጠቀለል የምሥጢር አንድነት
የማይከፋፈል የአካል ሦስትነት
ማን ይመረምራል የአንተን አምላክነት
ዕፁብ ማለት ብቻ ሥራህን በማየት
የማይጠቀለል የምሥጢር አንድነት
የማይከፋፈል የአካል ሦስትነት
ማን ይመረምራል የአንተን አምላክነት
ዕፁብ ማለት ብቻ ሥራህን በማየት
ልዑል ልዑል ዲበ ኪሩቤል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ብሩኅነታቸው ለውኃና ለእሳት
ጽሉምነታቸው ነፋስና መሬት
ነፋስና ውኃ በርጡብ ማንነት
ደረቅ ስለሆኑ መሬትና እሳት
አስማምተሃቸዋል በሰው ዓለምነት
ጽሉምነታቸው ነፋስና መሬት
ነፋስና ውኃ በርጡብ ማንነት
ደረቅ ስለሆኑ መሬትና እሳት
አስማምተሃቸዋል በሰው ዓለምነት
ልዑል ልዑል ዲበ ኪሩቤል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ሰማይን ያለ ዓምድ በላይ የዘረጋህ
ምድርን በውኃ ላይ አስፍተህ ያጸናህ
አክብረህ የሠራህ ሰውን ከምድር አፈር
በአርአያ በአምሳል እንተን መስሎ ሊኖር
ሞቱንም ሞትክለት ፍቅር እግዚአብሔር
ምድርን በውኃ ላይ አስፍተህ ያጸናህ
አክብረህ የሠራህ ሰውን ከምድር አፈር
በአርአያ በአምሳል እንተን መስሎ ሊኖር
ሞቱንም ሞትክለት ፍቅር እግዚአብሔር
ልዑል ልዑል ዲበ ኪሩቤል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
ወዐቢይ ወዐቢይ፪ ብሉየ መዋዕል፪
✦