የመላእክት አለቃ
✦
የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው
ሃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል
ሃይለ ልኡል ወልድም ስጋሽን ይለብሳል
በተለየ አካሉ ወደ አንቺ ይመጣል
ከስጋሽን ስጋ ከነፍስሽን ነፍስ ነስቶ ይዋሃዳል
በገጸ ህጻናት ካንቺ ይወለዳል
የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው
ሃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል
ደንቆሮ ሊሰማ ዲዶች ሊናገሩ
በጌታ ታምራት ዕውራን ሊበሩ
ሙታን ይነሱ ዘንድ በማህጸንሽ ፍሬ
ከእግዚአብሔር ወዳንቺ ተልኬያለሁ ዛሬ!
የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው
ሃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል!
ሃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል
ሃይለ ልኡል ወልድም ስጋሽን ይለብሳል
በተለየ አካሉ ወደ አንቺ ይመጣል
ከስጋሽን ስጋ ከነፍስሽን ነፍስ ነስቶ ይዋሃዳል
በገጸ ህጻናት ካንቺ ይወለዳል
የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው
ሃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል
ደንቆሮ ሊሰማ ዲዶች ሊናገሩ
በጌታ ታምራት ዕውራን ሊበሩ
ሙታን ይነሱ ዘንድ በማህጸንሽ ፍሬ
ከእግዚአብሔር ወዳንቺ ተልኬያለሁ ዛሬ!
የመላእክት አለቃ ገብርኤል ላከው
ሃያሉ እግዚአብሔር በሰማያት ያለው
የባህርይ ልጄ ወዳንቺ ይመጣል
ብለህ ለጽዮን ልጅ ንገራት ለድንግል!
✦