የመስቀሉ ፍቅር

የመስቀሉ ፍቅር /ነገር/ ቢገባን
እመቤታችንን እናያታለን
የመስቀሉ ፍቅር የገባቸዉ
እመቤታችን አለች ከጎናቸዉ
አባ ሕርያቆስ አባታችን
የመስቀሉ ነገር ቢገባዉ
ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር
ከእመቤቴ ጋራ ሲነጋገር
ከድንግል ማርያም ጋር ሲነጋገር
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችዉ
ተዋሐደ ስትል አማኑኤል አለችዉ
ሕሙማን ሲፈዉስ ኢየሱስ አለችዉ
ንጉሥ ነዉም ብላ ክርስቶስ አለችዉ
ተሰቅለ ስታየዉ መደኅኑ አለችዉ
ለመናኔዉ ጸሎት ልዮ ዕጣን
የዋሻዉ ሻማ ነሽ እመብርሃን
መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን /ከጽዮን/
ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን
ትርቢኝማለሽ ምን ልሁን
ድንግል እመቤቴ የእኔ እረዳት
ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሻል
የያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል
የእግዚአብሔር ሀገር የሚሉሽ
እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ
ቤተልሔም ስሄድ አይሻለሁ
ቀራንዮ ስሔድ አይሻለሁ
ፍጹም አትለይም ከልጅሽ
የአንቺስ ልዮ ነዉ ፍቅርሽ
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
← መዝሙር