የሚረዳን የለምና
✦
የሚረዳን የለምና ከኛ አትራቅ
ሚካኤል ሚካኤል በዓምደ ደመና
ፈጥነህ ቶሎ ና
ሚካኤል ሚካኤል በዓምደ ደመና
ፈጥነህ ቶሎ ና
ሁሉ ይወድሃል ያከብርሃል አንተን
ይዘህ ትወርዳለህ ይቅርታ ምሕረትን
የብርሃን መል አክ ሲገለጥ ብርሃንህ
የጨለማው ገዢ ወደቀ ከእግርህ
ይዘህ ትወርዳለህ ይቅርታ ምሕረትን
የብርሃን መል አክ ሲገለጥ ብርሃንህ
የጨለማው ገዢ ወደቀ ከእግርህ
በጎልጎታ ዋሻ ከግርጌ የቆምከው
የጌታን መነሣት ለዓለም ያበሠርከው
እኛም ልንነሣ ከሙታን መካከል
ሰብከኸናል አንተ ይኽን ታላቅ ወንጌል
የጌታን መነሣት ለዓለም ያበሠርከው
እኛም ልንነሣ ከሙታን መካከል
ሰብከኸናል አንተ ይኽን ታላቅ ወንጌል
ጳውሎስና ሲላስ ታሥረው ሲዘምሩ
በምልጃህ ተከፍቷል የተዘጋው በሩ
በመከራ ሆነው ሚካኤል ለሚሉ
ፈጥነህ ትደርሳለህ በኑሯቸው ሁሉ
በምልጃህ ተከፍቷል የተዘጋው በሩ
በመከራ ሆነው ሚካኤል ለሚሉ
ፈጥነህ ትደርሳለህ በኑሯቸው ሁሉ
ትንቢቱን ልታሳይ ወረድህ ወደ ፍጥሞ
ዮሐንስም አየ በመንፈስ ተገርሞ
መለከት ሲነፋ በዚያ አስፈሪ ቀን
ተወዳጁ መልአክ ሚካኤል ዋሰ ሁነን
ዮሐንስም አየ በመንፈስ ተገርሞ
መለከት ሲነፋ በዚያ አስፈሪ ቀን
ተወዳጁ መልአክ ሚካኤል ዋሰ ሁነን
✦