የምስራች ደስ ይበላችሁ
✦
የምሥራች ደስ ይበላችሁ፪
አሸብርቆ ዋለ ሙሽሮች ሠርጋችሁ፪
ሕይወታችሁ ሰላማዊ ፍጹም ፍቅር፪
እንደ ጽጌረዳ እንደአደይ ፈክቶ የሚኖር
አማኑኤል ያድርገው መልካም ትሥሥር
አዝ ---
መተሳሰብ መከባበር ይሁን ግብራችሁ፪
ሠርጐ እንዳይገባ ዲያብሎስ በትዳራችሁ
በጾም ጸሎት ይታጠር ሙሽሮች ጐጆአችሁ
አዝ ---
ዓይኖቻችሁ የጐረቤት አይመልከቱ፪
ለወሬ ለሐሜት ጆሮአችሁ አይከፈቱ
በችግር በደስታ በጾም ጸሎት በርቱ
አዝ ---
እግሮቻችሁ ይገስግሱ ወደእውነት፪
አማናዊ ማእድ ክርስቶስ ወዳለበት
በልባችሁ አኑሩት ታላቁን አባት
አዝ ---
ድንግል ማርያም ቅድስት እናት ለምኚላቸው፪
የሚፈልጉትን በሙሉ አንቺ አስጪያቸው
በሰማይ በምድርም ምልጃሽ አይራቃቸው
አሸብርቆ ዋለ ሙሽሮች ሠርጋችሁ፪
ሕይወታችሁ ሰላማዊ ፍጹም ፍቅር፪
እንደ ጽጌረዳ እንደአደይ ፈክቶ የሚኖር
አማኑኤል ያድርገው መልካም ትሥሥር
አዝ ---
መተሳሰብ መከባበር ይሁን ግብራችሁ፪
ሠርጐ እንዳይገባ ዲያብሎስ በትዳራችሁ
በጾም ጸሎት ይታጠር ሙሽሮች ጐጆአችሁ
አዝ ---
ዓይኖቻችሁ የጐረቤት አይመልከቱ፪
ለወሬ ለሐሜት ጆሮአችሁ አይከፈቱ
በችግር በደስታ በጾም ጸሎት በርቱ
አዝ ---
እግሮቻችሁ ይገስግሱ ወደእውነት፪
አማናዊ ማእድ ክርስቶስ ወዳለበት
በልባችሁ አኑሩት ታላቁን አባት
አዝ ---
ድንግል ማርያም ቅድስት እናት ለምኚላቸው፪
የሚፈልጉትን በሙሉ አንቺ አስጪያቸው
በሰማይ በምድርም ምልጃሽ አይራቃቸው
✦