የነቢያት ትንቢታቸው
✦
የነቢያት ትንቢታቸው የሀዋርያት ስብከታቸው
ማርያም ነሽ አክሊላቸው
መታረቂያ ሰነዳቸው
መና ያለብሽ ንፁ መሶብ
የመድኃኒት ምንጭ ለረሀብ
የዓለም ታሪክ ተለወጠ
እግዚአብሔር አንቺን ለእኛ ሰጠ
አዝ...........
መላዕክት ወጡ ወረዱብሽ
ሠማይና ምደር ታረቁብሽ
ስለሆንሽ የወርቅ መሰላል
ስምሽ ለትውልድ ከፍ ይላል
አዝ...........
የእኛ መለያ ነሽ ሰንደቅ
በከንቱ ምኞት ስንወድቅ
የምሕረት ዓመት መጣልን
የማይጠልቅ ፀሀይ ወጣልን
አዝ..........
ወልደሽ ስትሰጭን ንጉሱን
አየን ቀምሰነው ምህረቱን
አሁን ልጆቹ ተብለናል
የፀብ ግድግዳ ፈርሶልናል
አዝ............
ማርያም ነሽ አክሊላቸው
መታረቂያ ሰነዳቸው
መና ያለብሽ ንፁ መሶብ
የመድኃኒት ምንጭ ለረሀብ
የዓለም ታሪክ ተለወጠ
እግዚአብሔር አንቺን ለእኛ ሰጠ
አዝ...........
መላዕክት ወጡ ወረዱብሽ
ሠማይና ምደር ታረቁብሽ
ስለሆንሽ የወርቅ መሰላል
ስምሽ ለትውልድ ከፍ ይላል
አዝ...........
የእኛ መለያ ነሽ ሰንደቅ
በከንቱ ምኞት ስንወድቅ
የምሕረት ዓመት መጣልን
የማይጠልቅ ፀሀይ ወጣልን
አዝ..........
ወልደሽ ስትሰጭን ንጉሱን
አየን ቀምሰነው ምህረቱን
አሁን ልጆቹ ተብለናል
የፀብ ግድግዳ ፈርሶልናል
አዝ............
ዘማሪ ሲሳይ ወልደአረጋይ
✦