የነፍሳችን ቤዛ

የነፍሳችን ቤዛ የቅዱሳን ሀብት
ጸጋን የሚያሰጠን ጾም ነው መድኃኒት
የእስራኤል ልጆች በሙሴ ሲመሩ
በፍጹም ጸሎት ባሕርን ተሸገሩ
ቅዱሳን አባቶች ጾም ነው ጋሻቸው
ወደ ሕይወት መንገድ የሚመራቸው
ክፍላችን እንዲሆን ከቅዱሳን ጋራ
ፍቅር ቤ ችንን በጸሎት እንሥራ
ልባችንም ይሁን የጸሎት ጎዳና
የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድንወርስ በጠ?ና
← መዝሙር