የነገሥታት ንጉሥ

የነገሥታት ንጉሥ ቸሩ አባት
የጌቶቹም ጌታ በሰማያት
ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት
አዝ ---
ቅዳሜ በአንተ ዘንድ ቸሩ አባት
ምንም ቦታ የለው በሰማያት
ፍጹም ቸርነትህ ቸሩ አባት
የአንተ ባሕርይ ነው በሰማያት
ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት
አዝ ---
ምሕረትህ ለሰው ልጅ ቸሩ አባት
እጅጉን በዝታለች በሰማያት
ኃጢአት በበዛባት ቸሩአባት
ጸጋህ ትበዛለች በሰማያት
ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት
አዝ ---
የትእግሥት ብዛት ቸሩ አባት
እኔን ድንቆኛል በሰማያት
የኃጢአቴን ዋጋ ቸሩ አባት
መቼ ከፍለኸኛል በሰማያት
ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት
አዝ ---
ስንበድል ስንቀጥፍ ችሩ አባት
አንተ ተደብቀን በሰማያት
አይተህ እንዳላየህ ችሩ አባት
በምሕረት አለፍከን በሰማያት
ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት
አዝ ---
← መዝሙር