የኖኅ ቃል ኪዳኑ

የኖኅ ቃል ኪዳኑ ምልክት ዓርማው
የመዳኑ ምሥጢር የሰላም ተስፋው
እመቤቴ አንቺ ነሽ ቀስተደመናው
አንቺ የአሮን በትር ሳይተክላእት ያደገች
የማክሰኞ እርሻ ያለዘር ያፈራች
የሲና ሐመልማል የተዋሕዶ ምሥጢር
ክብርት እምቤቴ ሀገረ እግዚአብሔር
የዳዊት መሰንቆ ያሬድ ጽናጽል
የደካሞች ምርኩዝ የሰሎምን አኪሊል
ሰላሜ ተስፋዬ የሐዘኔ ደራሽ
የጽዮን ተራራ መሸሸጊዬ ነሽ
የኤልሳእ ማሠሮ ጨው የተገኘብሽ
የሕዝቅኤል ራእይ ንጽሕት አዳራሽ
አንቺ የአዳም ተስፋ የመዳኔ ብስራት
አንቀጸ ብርሃን የአማኑኤል እናት
← መዝሙር