የቅዱሳን አምላክ

አብርሃምን ከካራን የጠራኸዉ ጌታ
ለሙሴ በሲና የሆንከዉ መከታ
ልጠፋ ነዉና በሥጋ ፍላጎት
የይስሐቅም ጌታ ሕይወቴን ታደጋት
የኤርትራን ባሕር በኃይልህ የከፈልክ
በሲና በረሃ ሕዝብህን የመገብክ
ኖኅ ከጥፋት ዉኃ የዳነብህ አምላክ
ሎጥን እንዳዳንከዉ ፍጹም ምሕረትን ላክ
የተነበዮልህ ነቢያት በሙሉ
አምላክ ሰዉ ይሆናል ይወለዳል ሲሉ
ከዓሣ አንበሪ ሆድ ዮናስን ያወጣህ
ዓለም ልትዉጠኝ ነው አይለየኝ ጸጋህ
ሥጋን ተዋሕደህ በወሰንከዉ ሰዓት
የሞትክልኝ አምላክ ያዳንከኝ ከሞት ሞት
እንደወንጌልህ ሕግ የምኖር አድርገኝ
በመጨረሻዉ ቀን በቀኝህ አድርገኝ
አልቻልኩኝምና ልፈጽም ሕግህን
የሐዋርያት አጽናኝ ስጠኝ ብርታትህን
ምግባረ ጎደሎ ሆኛለሁኝና
የቅዱሳን አምላክ እርዳኝ እንድጸና
← መዝሙር