የቅዱሳን በአት
✦
ልቡና የሚመስጥ መዓዛ እጣኗ
ኅሊናን ይገዛል ዝማሬ ድጓዋ
የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
ቤ/ክ ናት አምባ መጠጊያቸው
የመላእከት ዜማ የአእዋፍ ዝማሬ
የሚለቀምባት የትሩፋት ፍሬ
አዝ -------------
ይዘምሩበታል በአንድነት ተባብረው
የሌዋዊው በትር ጸናጽል ከበሮው
አዝ -------------
ወራዳዋን ዓለም የናቋት በቅድሚያ
የእምነት አርበኞች ያገኝዋት በፍልሚያ
አዝ -----------------
መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው
ይፈውሳልና ተረፈ አጽማቸው
አዝ ----------------------
ከኃጥአን ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ
የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሀገሬ
ኅሊናን ይገዛል ዝማሬ ድጓዋ
የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው
ቤ/ክ ናት አምባ መጠጊያቸው
የመላእከት ዜማ የአእዋፍ ዝማሬ
የሚለቀምባት የትሩፋት ፍሬ
አዝ -------------
ይዘምሩበታል በአንድነት ተባብረው
የሌዋዊው በትር ጸናጽል ከበሮው
አዝ -------------
ወራዳዋን ዓለም የናቋት በቅድሚያ
የእምነት አርበኞች ያገኝዋት በፍልሚያ
አዝ -----------------
መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው
ይፈውሳልና ተረፈ አጽማቸው
አዝ ----------------------
ከኃጥአን ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ
የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሀገሬ
✦