የራማው ልዑል
✦
ራማው ልዑል ገብርኤል ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ብርሃን ለባሽ እሳታዊው መልአክ
አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ ፪
አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ ፪
የራማው ልዑል ገብርኤል ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
የምሥራች ነጋሪ ድንቅን ልደት አብሣሪ
የጽድቅ ፋና የድህነት ጎዳና ፪
የጽድቅ ፋና የድህነት ጎዳና ፪
የራማው ልዑል ገብርኤል ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ላመኑብህ ለተማጸኑብህ
ተጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ፪
ተጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ፪
የራማው ልዑል ገብርኤል ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው
ከእሳት ነበልባል የ አዳንካቸው፪
ከእሳት ነበልባል የ አዳንካቸው፪
የራማው ልዑል ገብርኤል ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ምሰሶ ዐምዳችን መጠጊያችን
ቅዱስ ገብርኤል ከለላችን፪
ቅዱስ ገብርኤል ከለላችን፪
የራማው ልዑል ገብርኤል ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ፪
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጆችህን ይምራን መንፈስህ ፪
ልጆችህን ይምራን መንፈስህ ፪
✦