የራሴን ፀጉር

የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራነኝ መችይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም
ስለምግብና ስለምለብሰው
ብዙ ብጨነቅ ጥቅሙ ምንድነው
አበባን ለምድር ምግብን ለወፎች
የሚሰጥ አባት አለኝ ሳይሰለች
የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራነኝ መችይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም
የማያምኑትን ስሙን ሳያውቁ
የሚያገኙትን ሳይጨነቁ
ስለምን ልድከም በከንቱ መሻት
እያለ ጌታ ያዳነኝ ከሞት
የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራነኝ መችይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም
የክፉዎች ሰልፍ ቢሰፍር በላዬ
ዝናሩን ታጥቆ ቢዝትገዳዬ
በሞት ጥላ ውስጥ ብጓዝ ብሔድም
የሚጠብቀኝ አያንቀላፋም
የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራነኝ መችይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም
ሀሳቤን ልጣል በእረኛዬ
በሚያሰማራኝ ቸር ጠባቂዬ
ከበረከት ምንጭአያሳጣኝም
በግ ስለራሱ ተጨንቆ አያውቅም
የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራነኝ መችይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም
መንግስቱን ልሻት ልፈልግ ፅድቁን
ስለሚሰጠኝ ጌታ ሌላውን
ስለሚጨነቅ ነገ ለራሱ
ላመስግን ዛሬ ታምኜ በእርሱ
የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራነኝ መችይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም
← መዝሙር