የሰው ልጅ በኃይልህ

የሰው ልጅ በኃይልህ ፈጽሞ አትመካ
አንድ አምላክ አለና በኃይሉ ኃይልን የሚለካ
አዝ ---
ኃይል አንደ ሶምሶን ከአምላክ ሲሰጥ እንጃ
በጉልበት መመካት ለማንም አይበከጂ
ሰናክሬም ቢነሳ በሕዝቅያስ ላይ
የደረሰበትን አልሰማህም ወይ
አዝ ---
ጎልያድ በኃይሉ ዳዊትን ቢንቀው
አዋረደው እንጂ ኃይሉ ምን ጠቀመው
እንደ ዳታንና እንደአቤሮን አይሆንም በግድ
ተመርጦ ነው እንጂ ለክብር በአምላክ ፈቃድ
ክህነትን ለአሮን ሕግንም ለሙሴ
ከሰው ሁሉ መርጠው ሰጧቸው ሥላሴ
← መዝሙር