የሾህ አክሊል
✦
የሾህ አክሊል ጉንጉን ደፍተው በራሱ ላይ
ብለው ዘበቱበት የአይሁድ ንጉሥ ሆይ
ብለው ዘበቱበት የአይሁድ ንጉሥ ሆይ
በጉልበታቸውም ተንበርከኩና
ሰላም ለአንተ ይሁን አሉት አፌዙና
ሰላም ለአንተ ይሁን አሉት አፌዙና
ራሳቸውንም እየነቀነቁ
መንገደኞች ሁሉ በጌታ ላይ ሳቁ
መንገደኞች ሁሉ በጌታ ላይ ሳቁ
አወይ ሌለውን ሰው ያድን የነበረው
ምነዋ ራሱን ሳያድን የቀረው
ምነዋ ራሱን ሳያድን የቀረው
እያሉ ሲነቅፉት በእርሱ ያላመኑ፪
ምልክት ከሰማይ ታየ ወዲያዉኑ፪
ምልክት ከሰማይ ታየ ወዲያዉኑ፪
ፀሐይም ጨለመ ደም ሆነች ጨረቃ፪
ከዋክብት ረገፉ ዓለት ሁሉ ነቃ፪
ከዋክብት ረገፉ ዓለት ሁሉ ነቃ፪
የመቅደሱ ግርዶሽ ከሁለት ሲቀደድ፪
የሞቱት ተነሡ ከመቃብር ጉድጓድ፪
የሞቱት ተነሡ ከመቃብር ጉድጓድ፪
✦