የሥላሴ መንበር

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሐል ሚካኤልንከፊት
አእላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት
እዩ ተመልከቱት የሰማዩን አባት
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ
በጽድቅ ሥራቸው ደምቀው ይ ያሉ
አዝ . . .
የቅዱሳን ኅብረት የቅዱሳን ሀገር
ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር
ጽድቅና ርኅራኄ የተሞላ ሰማይ
እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ
አዝ . . .
← መዝሙር