የጥበብ ሀገሯ
✦
የጥበብ ሃገሯ ወዴት ነው
ማደሪያዋስ ወዴት ነው፪
በውኑ ጎዳናዋ ከወዴት ተቃኘ
ዝናና ወሬዋ ከወዴት ተገኘ
ፈልጎ የገዛት ማነው በቀይ ወርቅ
ባሕሩን ታሻግሮ ስሟን በማወቅ
ማነው ያወረዳት ከደመና በላይ
ድምጻእንስ የሰማ ከላይ ከሰማይ
እርሷን የሚጠሉ ናቸውና ከንቱ
አይቀርላቸውም ኃላ የሞት ሞቱ፪
ሁሉን የሚያውቅ እርሱ ያውቃታል
የእውቀት ጎዳናዋ ያስተምርላታል
በክርሰቶስ ፈቃድ ምድር ላይ ታየች
ማደሪያዋስ ወዴት ነው፪
በውኑ ጎዳናዋ ከወዴት ተቃኘ
ዝናና ወሬዋ ከወዴት ተገኘ
ፈልጎ የገዛት ማነው በቀይ ወርቅ
ባሕሩን ታሻግሮ ስሟን በማወቅ
ማነው ያወረዳት ከደመና በላይ
ድምጻእንስ የሰማ ከላይ ከሰማይ
እርሷን የሚጠሉ ናቸውና ከንቱ
አይቀርላቸውም ኃላ የሞት ሞቱ፪
ሁሉን የሚያውቅ እርሱ ያውቃታል
የእውቀት ጎዳናዋ ያስተምርላታል
በክርሰቶስ ፈቃድ ምድር ላይ ታየች
እነሆ ቤት ሠራች ሰባ አምድ አቆመች፪
ጥበብ ግን እርሱ ነው መድኃኒታችን
በሥጋ ተገልጦ እኛን አዳነን
በደሙ ፈወሶ ተወዳጅን
ለእርሱ የመረጠን ይክበር ይመስገን ፪
ጥበብ ግን እርሱ ነው መድኃኒታችን
በሥጋ ተገልጦ እኛን አዳነን
በደሙ ፈወሶ ተወዳጅን
ለእርሱ የመረጠን ይክበር ይመስገን ፪
✦